Isaiah 52

1ጽዮን ሆይ፤ ተነሺ፤ ተነሺ፤
ኀይልን ልበሺ፤
ቅድስቲቱ ከተማ፤ ኢየሩሳሌም ሆይ!
የክብር ልብስሽን ልበሺ፤
ያልተገረዘ የረከሰም
ከእንግዲህ ወደ አንቺ አይገባም።
2ትቢያሽን አራግፊ፤
ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ተነሺ በዙፋንሽ ላይ ተቀመጪ፤
ምርኮኛዪቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፤
የዐንገትሽን የእስራት ሰንሰለት አውልቀሽ ጣዪ።
3 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“ያለ ዋጋ ተሸጣችሁ ነበር፤
ያለ ገንዘብ ትቤዣላችሁ።”
4ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“በመጀመሪያ ሕዝቤ ይኖር ዘንድ ወደ ግብፅ ወረደ፤
በኋላም አሦር ያለ ምክንያት አስጨንቆ ገዛው።
5“አሁን እዚህ ምን አለኝ?” ይላል እግዚአብሔር

“ሕዝቤ ያለ ምክንያት ተወስዷል፤
የገዟቸው ተሣልቀውባቸዋል”
የሙት ባሕር ጥቅሎችና ቩልጌት ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ የማሶሬቱ ቅጅ ግን፣ ሙሾ ይላል።

ይላል እግዚአብሔር

“ቀኑን ሙሉ፣
ስሜ ያለ ማቋረጥ ይሰደባል።
6ስለዚህ ሕዝቤ ስሜን ያውቃል፤
በዚያ ቀንም፣
አስቀድሜ የተናገርሁ እኔ መሆኔን ይረዳል፤
እነሆ፤ እኔው ነኝ።”

7በተራሮች ላይ የቆሙ፣
የምሥራች ይዘው የሚመጡ እግሮች፣
ሰላምን የሚናገሩ፣
መልካም ዜና የሚያበሥሩ፣
ድነትን የሚያውጁ፣
ጽዮንንም፣
“አምላክሽ ነግሧል” የሚሉ እንዴት ያማሩ ናቸው።
8ስሚ፤ ጠባቂዎችሽ ድምፃቸውን ከፍ አድርገዋል፤
በአንድነት በእልልታ ይዘምራሉ።
እግዚአብሔር ወደ ጽዮን ሲመለስ፣
በዐይኖቻቸው ያያሉ።
9እናንት የኢየሩሳሌም ፍርስራሾች፣
በአንድነት በእልልታ ዘምሩ፤
እግዚአብሔር ሕዝቡን አጽናንቷል፤
ኢየሩሳሌምንም ተቤዥቷልና።
10 እግዚአብሔር በመንግሥታት ሁሉ ፊት፣
የተቀደሰ ክንዱን ይገልጣል፤
በምድር ዳርቻዎች ያሉ ሁሉ፣
የአምላካችንን ማዳን ያያሉ።

11እናንት የእግዚአብሔርን ዕቃ የምትሸከሙ፣
ተለዩ፤ ተለዩ፤ ከዚያ ውጡ፤
ርኩስ ነገር አትንኩ፤
ከዚያ ውጡ ንጹሓንም ሁኑ።
12ሆኖም በችኰላ አትወጡም፤
ሸሽታችሁም አትሄዱም፤
እግዚአብሔር ፊት ፊታችሁ ይሄዳል፤
የእስራኤል አምላክ ደጀን ይሆናችኋል።

የባሪያው ሥቃይና ክብር

13እነሆ፤ ባሪያዬ የሚያከናውነው በማስተዋል ነው፤
ወይም ባሪያዬ ይበለጽጋል

ገናና ይሆናል፤ ከፍ ከፍ ይላል፤ እጅግ ይከብራልም።
14ብዙዎች በእርሱ
ዕብራይስጡ፣ በአንተ ይላል።
እስኪደነግጡ ድረስ፣
መልኩ ከማንም ሰው ተለየ፤
ከሰው ልጆችም ሁሉ ይልቅ ተጐሳቈለ።
15ስለዚህ ብዙ መንግሥታትን ያስደንቃል፤
በእርሱ ምክንያት ነገሥታት አፋቸውን ይይዛሉ፤
ያልተነገራቸውን ያያሉ፤
ያልሰሙትን ያስተውላሉ።
Copyright information for AmhNASV